1 ተሰሎንቄ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፥ እርሱም መቀደሳችሁ፥ ከዝሙትም መራቃችሁ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ፈቃድ እናንተ እንድትቀደሱና ከዝሙት እንድትርቁ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ |
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።
መልካም፥ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
እንደገና ስመጣ በእናንተ ፊት አምላኬ ያዋርደኝ ይሆን እያልኩ፥ ከዚህ በፊት ስለ ሠሩት ኃጢአትና ስለ ፈጸሙትም ርኩሰት፥ ዝሙትና መዳራት ንስሓ ሳይገቡ ቀርተው እንዳላዝን እፈራለሁ።
ስለዚህ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን በመንፈሳዊ ጥበብና ማስተዋል ሁሉ የፈቃዱን እውቀት እንድትሞሉ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም፤
እንግዲህ በእናንተ ያሉትን ምድራዊ ነገሮች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም፦ “ዝሙትና ርኩሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ ስግብግብነት” ናቸው፤
ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል።
የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከመጀመሪያው አንሥቶ በመንፈስ በመቀደስና በእውነት በማመን እንድትድኑ መርጦአችኋልና፤
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ትፈጽሙ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ያወቃችሁ፥ በመንፈስ የተቀደሳቹ፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትታዘዙና በደሙም ትረጩ ዘንድ ለተመረጣችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”