Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤፌሶን 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባርያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ለታይታና ከእነርሱ ሙገሳን ለማግኘት ሳይሆን፣ እንደ ክርስቶስ ባሮች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከልብ በመፈጸም ታዘዟቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የምትታዘዙትም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከልብ እንደሚፈጽሙ እንደ ክርስቶስ አገልጋዮች ሆናችሁ ነው እንጂ ሰውን ደስ ለማሰኘት ብላችሁ ለታይታ አይሁን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርጉ እንደ ክር​ስ​ቶስ ባሮች እንጂ ለሰው ደስ እን​ደ​ሚ​ያ​ሰኝ ለታ​ይታ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ።

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 6:6
20 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ወንጌል በአደራ እንዲሰጠን እግዚአብሔር የታመንን እንዳደረገን፥ እንዲሁ ሰውን ደስ ለማሰኘት ሳይሆን ልባችንን የሚመረምረውን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ብለን እንናገራለን።


አሁን ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሳምናለሁን? ወይስ ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? እስከ አሁን ሰውን ደስ የማሰኝ ብሆን ኖሮ የክርስቶስ ባርያ አልሆንም ነበር።


ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።


ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት አትኑሩ።


ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ ይበልጥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤


በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ፥ እኅቴም እናቴም ነውና።”


በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ትፈጽሙ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ ጽናት ያስፈልጋችኋል።


ስለዚህ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን በመንፈሳዊ ጥበብና ማስተዋል ሁሉ የፈቃዱን እውቀት እንድትሞሉ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም፤


በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚፈጽም እንጂ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት አይገባም።


ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዓለም ይኖራል።


አስቀድማችሁ የኃጢአት ባርያዎች የነበራችሁ፥ ነገር ግን ለተሰጣችሁለት የትምህርት ዓይነት ከልባችሁ በመታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።


ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል።


እኔም ጌታ እንደሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉና፥ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።


በዚህ መንገድ መልካም በማድረግ የሞኞችን አላዋቂነት ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።


በዚህም ሁሉ ግን አታላይቱ ይሁዳ በሐሰት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም፥ ይላል ጌታ።


ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፥ እርሱም መቀደሳችሁ፥ ከዝሙትም መራቃችሁ ነው፤


የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ፥ እኅቴም፥ እናቴም ነው” አለ።


ባርያ ሆኖ ሳላ በጌታ የተጠራ የጌታ ነጻ ነውና፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ ሳለ የተጠራ የክርስቶስ ባርያ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios