La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 9:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በነጋም ጊዜ በማለዳ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፥ “ላሰናብትህ ስለሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፥ ከሳሙኤል ጋር ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በማለዳ ተነሡ፤ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፣ “ላሰናብትህ ስለ ሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፣ ከሳሙኤል ጋራ ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በነጋም ጊዜ ማለዳ ሳሙኤል ከሰገነቱ ላይ ሳኦልን ጠርቶ “እንግዲህ ተነሥ፤ ላሰናብትህና መንገድህን ቀጥል” አለው፤ ሳኦልም ከመኝታው ተነሣ፤ እርሱና ሳሙኤልም አብረው ወደ መንገዱ ሄዱ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ በነ​ጋም ጊዜ ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን፥ “ከሰ​ገ​ነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነ​ሣና ላሰ​ና​ብ​ትህ” አለው። ሳኦ​ልም ተነሣ፤ እር​ሱና ሳሙ​ኤ​ልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማልዶም ተነሡ፥ በነጋም ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነሣና ላስናብትህ አለው። ሳኦልም ተነሣ፥ እርሱና ሳሙኤልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 9:26
6 Referencias Cruzadas  

ሎጥም ወጣ፥ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም ነገራቸው፥ አላቸውም፦ ተነሡ፥ ከዚህ ስፍራ ውጡ፥ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። አማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።


ከከተማው ምንም ያህል ርቀው ሳይሄዱ፥ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፦ “እነዚያን ሰዎች ቶሎ ድረስባቸውና፥ ‘ለበጎ ነገር ስለምን ክፉ መለሳችሁ?


ተነሣና ሕዝቡን ቀድስ፥ እንዲህም በላቸው፦ ‘እስከ ነገ ተቀደሱ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፦ “እስራኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፤ እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።”


ሌዋዊውም፥ “በይ ተነሺና እንሂድ” አላት፤ ነገር ግን መልስ አልነበረም። ከዚያም በአህያው ላይ ከጫናት በኋላ ወደ ቤቱ ጉዞውን ቀጠለ።


ከማምለኪያው ኰረብታ ወደ ከተማዪቱ ከወረዱ በኋላ ሳሙኤል በቤቱ ሰገነት ላይ ከሳኦል ጋር ተነጋገረ።


ወደ ከተማዪቱ ዳርቻ እየወረዱ ሳለ፥ ሳሙኤል ሳኦልን፥ “አገልጋይህ ወደ ፊት ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው፤ አገልጋይህም እንዳለፈ፥ አንተ ግን ከጌታ የተላከ መልእክት እንድነግርህ ለጥቂት ጊዜ እዚህ ቆይ” አለው።