La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 8:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የበኩር ልጁ ስም ኢዩኤል ሲሆን፥ የሁለተኛው ልጁ ስም አቢያ ነበረ፤ እነርሱም በቤርሳቤህ ይፈርዱ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የበኵር ልጁ ኢዮኤል ሲሆን፣ ሁለተኛው ልጁ አብያ ነበረ፤ እነርሱም በቤርሳቤህ ይፈርዱ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የበኲር ልጁ ኢዩኤል፥ ታናሽ ልጁ አቢያ ተብለው የሚጠሩ ሲሆኑ በቤርሳቤህ ዳኞች ሆነው ተሾመው ነበር፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የል​ጆ​ቹም ስሞች እነ​ዚህ ነበሩ። የበ​ኵር ልጁ ስም ኢዩ​ኤል፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም አብያ ነበረ። እነ​ር​ሱም በቤ​ር​ሳ​ቤህ ፈራ​ጆች ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የበኩር ልጁም ስም ኢዮኤል፥ የሁለተኛውም ስም አብያ ነበረ። እነርሱም በቤርሳቤህ ይፈርዱ ነበር።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 8:2
7 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰ፥ ተነሥተውም ወደ ቤርሳቤህ አብረው ሄዱ፥ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ።


እስራኤልም ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፥ ወደ ቤርሳቤህ ደረሰ፥ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ።


ኤልያስም ስለ ፈራ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአገልጋዩ ጋር በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ከተማ ሄደ። አገልጋዩንም በዚያ ተወው።


ሰሎምም ኬልቅያስን ወለደ፤ ኬልቅያስም ዓዛርያስን ወለደ፤


የሳሙኤልም ልጆች፤ በኩሩ ኢዮኤል፥ ሁለተኛውም አብያ ነበሩ።


የይስዓር ልጅ፥ የቀዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ነበር።


ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም ከንቱ ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፥ ወደ ጌልገላም አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ።”