La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 30:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ትንሽም ሆነ ትልቅ፥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆች፥ ምርኮም ሆነ ሌላ፥ አማሌቃውያን ከወሰዱት ነገር ምንም የጐደለ አልነበረም። ዳዊት ሁሉንም አስመለሰ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆች፣ ምርኮም ሆነ ሌላ፣ አማሌቃውያን ከወሰዱት ነገር ምንም የጐደለ አልነበረም፤ ዳዊት ሁሉንም አስመለሰ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንድም የጐደለ ሳይኖር ዳዊት የተከታዮቹን ወንዶችና ሴቶች ልጆች፥ እንዲሁም ዐማሌቃውያን ማርከው የወሰዱትን ምርኮ ሁሉ አስመለሰ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከወ​ን​ዶ​ችና ከሴ​ቶች ልጆች፥ ከወ​ሰ​ዱት ምርኮ ሁሉ፥ ታላ​ቅም ሆነ፥ ታና​ሽም ሆነ፥ ምንም የተ​ወ​ላ​ቸው የለም፤ ዳዊ​ትም ሁሉን አስ​ጣለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች፥ ከወሰዱትም ምርኮ ሁሉ፥ ታላቅም ሆነ ታናሽም ሆነ፥ ምንም የጎደለባቸው የለም፥ ዳዊትም ሁሉን አስጣለ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 30:19
8 Referencias Cruzadas  

እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ንብረቱም በምድር ላይ በዝቶአል።


ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ወደ ጦርነት የወጡትን ከእጃችን በታች ያሉትን ቈጥረናል፥ ከእኛ አንድም ሰው አልጐደለም።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፥ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።


እንዲሁም ዳዊት የበጉን፥ የፍየሉንና የላሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ፤ ሰዎቹም “ይህ የዳዊት ምርኮ ነው” እያሉ መንጋውን ከሌሎች ከብቶች ፊት ለፊት ይነዱ ነበር።


ዳዊትም፥ “ይህን ወራሪ ሠራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?” ሲል ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “በእርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተላቸው!” ሲል መለሰለት።