La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 28:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ምክንያቱም አንተ ለጌታ ቃል ታዛዥ ሆነህ አልተገኘህም፤ዐማሌቃውያንና የእነርሱ የሆነውንም ሁሉ አልደመሰስክም፤ ስለዚህ ጌታ አሁን ይህን ሁሉ አደረገብህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለእግዚአብሔር ስላልታዘዝህ፣ ታላቅ ቍጣውንም በአማሌቃውያን ላይ ስላልፈጸምህ እግዚአብሔር ዛሬ ይህን አድርጎብሃል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንተ ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዥ ሆነህ አልተገኘህም፤ ዐማሌቃውያንና የእነርሱ የሆነውንም ሁሉ አልደመሰስክም፤ እንግዲህ እግዚአብሔር አሁን ይህን ሁሉ የሚያደርግብህ በዚህ ምክንያት ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ህ​ምና፥ በአ​ማ​ሌ​ቅም ላይ ታላቅ የሆነ ቍጣ​ውን አላ​ደ​ረ​ግ​ህ​ምና ስለ​ዚህ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር አድ​ር​ጎ​ብ​ሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማህምና፥ በአማሌቅም ላይ ታላቅ የሆነ ቁጣውን አላደረግህምና ስለዚህ ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ነገር አድርጎብሃል።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 28:18
9 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ያ ነቢይ ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ጌታ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘እኔ ይገደል’ ብዬ የፈረድኩበትን ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል።”


እንዲሁ ሳኦል በጌታ ላይ ስላደረገው ኃጢአት፥ የጌታንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ ስለ ጠየቀ፥


የጌታን ሥራ በቸልታ የሚያደርግ ርጉም ይሁን፥ ደም ከማፍሰስም ሰይፉን የሚከለክል ርጉም ይሁን።


በዚህ ጊዜ ሳኦል፥ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕቱን አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።


ሳኦልም መልሶ እንዲህ አለ፤ “የጌታን ቃል ታዝዣለሁ፤ ጌታ በላከኝ መሠረት ሄጃለሁ፤ አማሌቃውያንን በሙሉ አጥፍቼ ንጉሣቸውን አጋግን አምጥቻለሁ።


ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ጌታ የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።


ነገር ግን ሳኦልና ሠራዊቱ አጋግን፥ ምርጥ ምርጡን በግና የቀንድ ከብት፥ የሰባውን ጥጃና ጠቦት፥ መልካም የሆነውን ሁሉ ሳይገድሉ ተውት። እነዚህን ፈጽመው ለማጥፋት ፈቃደኞች አልነበሩም፤ ነገር ግን የተናቀውንና የማይጠቅመውን ሁሉ አጠፉ።