Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 28:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ለእግዚአብሔር ስላልታዘዝህ፣ ታላቅ ቍጣውንም በአማሌቃውያን ላይ ስላልፈጸምህ እግዚአብሔር ዛሬ ይህን አድርጎብሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ምክንያቱም አንተ ለጌታ ቃል ታዛዥ ሆነህ አልተገኘህም፤ዐማሌቃውያንና የእነርሱ የሆነውንም ሁሉ አልደመሰስክም፤ ስለዚህ ጌታ አሁን ይህን ሁሉ አደረገብህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አንተ ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዥ ሆነህ አልተገኘህም፤ ዐማሌቃውያንና የእነርሱ የሆነውንም ሁሉ አልደመሰስክም፤ እንግዲህ እግዚአብሔር አሁን ይህን ሁሉ የሚያደርግብህ በዚህ ምክንያት ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ህ​ምና፥ በአ​ማ​ሌ​ቅም ላይ ታላቅ የሆነ ቍጣ​ውን አላ​ደ​ረ​ግ​ህ​ምና ስለ​ዚህ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር አድ​ር​ጎ​ብ​ሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማህምና፥ በአማሌቅም ላይ ታላቅ የሆነ ቁጣውን አላደረግህምና ስለዚህ ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ነገር አድርጎብሃል።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 28:18
9 Referencias Cruzadas  

ነቢዩም ንጉሡን አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ ፈጽሞ ይገደል ያልሁትን ሰው ለቅቀኸዋልና በገመዱ ትገባለህ፤ በሕዝቡም ፈንታ ያንተ ሕዝብ በገመዱ ይገባል።’ ”


ሳኦል ለእግዚአብሔር ስላልታመነ ሞተ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልጠበቀም፤ ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤


“የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያከናውን ርጉም ይሁን፤ ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚከላከል የተረገመ ይሁን!


በዚህ ጊዜ ሳኦል፣ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕቱን አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።


ሳኦልም ሳሙኤልን መልሶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ፤ እግዚአብሔር በላከኝ መሠረት ሄጃለሁ፤ አማሌቃውያንን በሙሉ አጥፍቼ ንጉሣቸውን አጋግን አምጥቻለሁ።


ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።


ነገር ግን ሳኦልና ሰራዊቱ አጋግን፣ ምርጥ ምርጡን በግና የቀንድ ከብት፣ የሰባውን ጥጃና ጠቦት፣ መልካም የሆነውን ሁሉ ሳይገድሉ ተውት። እነዚህን ፈጽመው ለማጥፋት ፈቃደኞች አልነበሩም፤ ነገር ግን የተናቀውንና የማይጠቅመውን ሁሉ አጠፉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos