ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፥ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።
1 ሳሙኤል 25:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፥ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በጌታ ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፥ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፣ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፣ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው በአንተ ላይ አደጋ ጥሎ ሊገድልህ ቢፈልግ አንድ ሰው ውድ የሆነ ሀብቱን እንደሚጠብቅ አምላክህ እግዚአብሔር አንተን በሰላም ይጠብቅሃል፤ ስለ ጠላቶችህም የሆነ እንደ ሆነ አንድ ሰው ድንጋዩን ከወንጭፍ እንደሚያስፈነጥር እግዚአብሔር ራሱ አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያሳድድህና ነፍስህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌታዬ ነፍስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሕይወት ማሰሪያ የታሰረች ትሆናለች፤ የጠላቶችህ ነፍስ ግን በወንጭፍ እንደሚወነጨፍ ትሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያሳድድህ ዘንድ ነፍስህንም ይሻ ዘንድ ሰው ቢነሣ፥ የጌታዬ ነፍስ በሕያዋን ወገን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የታሰረች ትሆናለች፥ የጠላቶችህንም ነፋስ ከወንጭፍ እንደሚጣል እንዲሁ ይጥላታል። |
ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፥ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።
የኢያቡስቴንም ራስ ወደ ኬብሮን ዳዊት ዘንድ አምጥተው ንጉሡን፥ “አንተን ሊገድል ይፈልግ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ፤ እነሆ ጌታ በዛሬው ቀን ስለ ጌታዬ ስለ ንጉሡ ሳኦልንና ዘሩን ተበቅሎአል” አሉት።
ይህም ሁሉም አንድ እንዲሆኑ፥ አንተም፥ አባት ሆይ! በእኔ እንዳለህና እኔም በአንተ እንዳለሁ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ እንዲሆኑ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ ዓለም እንዲያምን ነው።
ይህም እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በፍጹም አንድ እንዲሆኑ፥ እንዲሁም አንተ እንደ ላክኸኝና በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ዓለም እንዲያውቅ ነው።
እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፥ በጌታ የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፥ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።”