La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 24:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለሰዎቹም፥ “ጌታ በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ከማድረግና ጌታ የቀባው ስለ ሆነም እጄን በእርሱ ላይ ከማንሣት ጌታ ይጠብቀኝ” አላቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት ሰዎቹን በዚህ ቃል ገሠጻቸው፤ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ከዋሻው ወጥቶ ሄደ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህም አባባሉ በሳኦል ላይ አደጋ እንዳይጥሉበት ዳዊት ተከታዮቹን ከለከላቸው። ሳኦልም ከዚያ በመነሣት ከዋሻው ወጥቶ ሄደ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባው ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው በጌ​ታዬ ላይ እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር አደ​ርግ ዘንድ፥ እጄ​ንም እጥ​ል​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ያር​ቀው” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም በዚህ ቃል ሰዎቹን ከለከላቸው፥ በሳኦልም ላይ ይነሡ ዘንድ አልተዋቸውም፥ ሳኦልም ከዋሻው ተነሥቶ መንገዱን ሄደ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 24:7
10 Referencias Cruzadas  

ዳዊትም፥ “ታዲያ ጌታ የቀባውን ለማጥፋት እጅህን ስታነሣ እንዴት አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው።


አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህ አድርጌ ከሆነ፥ ዓመፃም በእጄ ቢኖር፥


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤


እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”


ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቁረጡ ልቡ በኀዘን ተመታ።


ዳዊት ሰዎቹን በዚህ ቃል ከለከላቸው፤ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ከዋሻው ወጥቶ ሄደ።


ደም እንዳላፈስና በገዛ እጄ እንዳልበቀል ዛሬ ስለ ጠበቅሽኝ ስለ በጎ ሐሳብሽ አንቺም የተባረክሽ ሁኚ።


ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና እንደ ታማኝነቱ ይክፈለው። እኔ ግን ዛሬ አንተን ጌታ በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ ጌታ በቀባው ላይ እጄን አላነሣሁም።


ዳዊት ግን አቢሳን እንዲህ አለው፤ “አትግደለው! ጌታ በቀባው ላይ እጁን አንሥቶ ከበደል ነጻ የሚሆን ማን ነው?