1 ሳሙኤል 22:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፤ “የአኪጦብ ልጅ ሆይ፤ እንግዲህ ስማ” አለው። አቢሜሌክም፥ “እሺ ጌታዬ” ብሎ መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፤ “የአኪጦብ ልጅ ሆይ፤ እንግዲህ ስማ” አለው። አቢሜሌክም፣ “ዕሺ ጌታዬ” ብሎ መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም፥ “የአሒጡብ ልጅ ሆይ! እንግዲህ ስማ” አለው። አቤሜሌክም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” ብሎ መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “የአኪጦብ ልጅ ሆይ! እንግዲህ ስማ” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ ጌታዬ ሆይ” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ የአኪጦብ ልጅ ሆይ፥ እንግዲህ ስማ አለ፥ እርሱም፦ እነሆኝ፥ ጌታዬ ሆይ ብሎ መለሰ። |
የሳኦል ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ወደ ዳዊት በመጣ ጊዜ፥ በግምባሩም ወድቆ እጅ ነሣ። ዳዊትም፥ “መፊቦሼት!” ብሎ ጠራው። እርሱም፥ “እነሆ፤ አገልጋይህ” አለ።
ከዚያም ንጉሡ፥ የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቢሜሌክን፥ በኖብ ካህናት የነበሩትን የአባቱን ቤተሰብ በሙሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ሁሉም ወደ ንጉሡ መጡ።
ሳኦልም፤ “ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ፥ በእኔ ላይ እንዲያምፅብኝና እንዲያደባብኝ፥ እንጀራና ሰይፍ በመስጠት፥ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ በመጠየቅ ከእሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለታችሁብኝ?” አለው።
ሳኦልም እንዲህ አላቸው፤ “እናንት የብንያም ሰዎች ስሙ! በውኑ የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ ሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋችኋልን?