La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 20:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ምስክር ይሁን! ነገ በዚህ ሰዓት ወይም በሦስተኛው ቀን፥ ስለ አንተ መልካም አስተሳሰብ ያለው መሆኑን አባቴን ጠይቄ ከተረዳሁ በኋላ፥ ስለዚሁ ጉዳይ የሚገልጥልህ መልእክተኛ እልክብሃለሁ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁንብኝ፤ አባቴን ነገ መርምሬ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በዚህ ሰዓት እልክብሃለሁ፤ ስለ አንተ ያለው አመለካከት በጎ ከሆነም አሳውቅሃለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ሰዓት ወይም በሦስተኛው ቀን ስለ አንተ መልካም አስተሳሰብ ያለው መሆኑን አባቴን ጠይቄ ከተረዳሁ በኋላ ስለዚሁ ጉዳይ የሚገልጥልህ መልእክተኛ እልክብሃለሁ፤ ለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁን!

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል፤ እስከ ሦስት ቀን ድረስ በዚህ ጊዜ አባ​ቴን መር​ምሬ እነሆ፥ በዳ​ዊት ላይ መል​ካም ቢያ​ስብ፥ እነሆ፥ ወደ ሜዳ ወደ አንተ አል​ል​ክም፤ ይህም ምል​ክት ይሁ​ንህ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮናታንም ዳዊትን አለው፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁን፥ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በዚህ ጊዜ አባቴን መርምሬ፥ እነሆ፥ በዳዊት ላይ መልካም ቢያስብ ልኬ እገልጥልሃለሁ፥

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 20:12
10 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በጌታ ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፥ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን ከሞት አተረፈ።


መንገዴን አያይምን? እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?”


ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፥ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም።


ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውኃ ነው፥ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።


“የአማልክት አምላክ ጌታ! የአማልክት አምላክ ጌታ! እርሱ አውቆታል፥ እስራኤልም ራሱ ይወቀው፤ በጌታ ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደሆነ ዛሬ አታድነን፤


ዮናታን፥ “ና! ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው፤ ተያይዘውም ወጡ።


ነገር ግን አባቴ ክፉ አስቦብህ፥ ይህን ሳላሳውቅህ ብቀርና በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ፥ ጌታ ክፉ ያድርግብኝ፤ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ። ጌታ ከአባቴ ጋር እንደ ነበር እንደዚሁ ከአንተም ጋር ይሁን።


ሁለቱም በጌታ ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ። ከዚያም ዮናታን ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊት ግን እዚያው ሖሬሽ ተቀመጠ።