1 ሳሙኤል 17:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልና እስራኤላውያን ደግሞ ተሰብስበው በዔላ ሸለቆ ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንንም ለመግጠም ተሰለፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልና እስራኤላውያን ተሰብስበው፣ በኤላ ሸለቆ ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንንም ለመግጠም ቦታ ቦታቸውን ያዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልና እስራኤላውያንም ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት በተዘጋጁበት በኤላ ሸለቆ ተሰብስበው መሸጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልና የእስራኤል ሰዎችም ተሰበሰቡ፤ በኤላ ሸለቆም ሰፈሩ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጉ ተሰለፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ተከማቹ፥ በዔላ ሸለቆም ሰፈሩ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጉ ተሰለፉ። |
ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ አንተ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እዚህ አለ፤ ከኤፉዱ በስተ ኋላ በጨርቅ ተጠቅልሏል፥ እነሆ፥ ከፈለግህ ውሰደው፤ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ሰይፍ እዚህ የለም” ብሎ መለሰለት። ዳዊትም “እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱኑ ስጠኝ” አለው።