በሰማይ ሆነህ ስማ፥ አድርግም፥ ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፤ ስለአካሄዱም ቅጣው፤ ንጹሑንም ነጻ አውጣው፥ እንደ ጽድቁም ክፈለው።
1 ነገሥት 8:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ በደላቸውን ይቅር በል፤ እርዳቸው፤ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን ሐሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ይቅር በል፤ አድርግም። የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ የምታውቅ አንተ ብቻ ስለ ሆንህ ልቡን ለምታውቀው ለእያንዳንዱ ሰው እንደ አካሄዱ ክፈለው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጸሎታቸውን ስማ፤ በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን በመስማት በደላቸውን ይቅር በላቸው፤ ርዳቸውም፤ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን ሐሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአባቶቻችን በሰጠሃት ምድር ላይ በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ይፈሩህ ዘንድ፥ በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና፥ ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው። |
በሰማይ ሆነህ ስማ፥ አድርግም፥ ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፤ ስለአካሄዱም ቅጣው፤ ንጹሑንም ነጻ አውጣው፥ እንደ ጽድቁም ክፈለው።
አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የሚሄዱበትንም መልካም መንገድ በማሳየት የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።
ልብን የሚያሸብር መራር ኀዘን ደርሶባቸው፥ ከማንም ሰው ወይም ከሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ቤተ መቅደስ እጃቸውን በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፥
በዚህም ዓይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ።
“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።
በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፥ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለው።
ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እያንዳንዱን ሰው እንደ መንገዱ እፈርዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ተመለሱ፥ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
ለሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ለሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም “በጎቼን አሰማራ።
ሲጸልዩም “የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ! ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው፤” አሉ።
“የአማልክት አምላክ ጌታ! የአማልክት አምላክ ጌታ! እርሱ አውቆታል፥ እስራኤልም ራሱ ይወቀው፤ በጌታ ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደሆነ ዛሬ አታድነን፤
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
ጌታ ግን ሳሙኤልን፥ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። ጌታ የሚያየው፥ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ ጌታ ግን ልብን ያያል” አለው።