1 ነገሥት 6:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፥ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ሲሆን በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበደ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅድስተ ቅዱሳኑም ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ ከዝግባ የተሠራውንም መሠዊያ በወርቅ ለበጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፥ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ሲሆን በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበደ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቅድስተ ቅዱሳኑም ርዝመት ሃያ ክንድ፥ ስፋቱም ሃያ ክንድ፥ ቁመቱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ በጥሩም ወርቅ ለበጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቅድስተ ቅዱሳንም ርዝመት ሃያ ክንድ፥ ስፋቱም ሃያ ክንድ ቁመቱም ሀያ ክንድ ነበረ፤ በጥሩ ወርቅም ለበጠው። |
ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን በውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ እርሱም በወርቅ በተለበጠው ውስጠኛ ክፍል መግቢያ በር ክፈፉንም በተሸጋገሩ የወርቅ ሰንሰለቶች አስጌጠው።
ለጌታ ቤት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰሎሞን የሚከተሉትን ዕቃዎች አሠራ፤ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ።
ከእንጨት የተሠራው መሠዊያ ቁመቱ ሦስት ክንድ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ነበር፥ ማዕዘኖቹ፥ እግሩና ግድግዳው ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ እርሱም፦ “ይህ በጌታ ፊት ያለ ገበታ ነው” አለኝ።