1 ነገሥት 4:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሒሻር የተባለው፦ የቤተ መንግሥት አገልጋዮች ኀላፊ፤ አዶኒራም የተባለው የዓብዳ ልጅ፦ የግዳጅ ሥራ ተቆጣጣሪ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሒሳር፣ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፤ የዓብዳ ልጅ አዶኒራም የግዳጅ ሥራ ተቈጣጣሪ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሒሻር የተባለው፦ የቤተ መንግሥት አገልጋዮች ኀላፊ፤ አዶኒራም የተባለው የዓብዳ ልጅ፦ የግዳጅ ሥራ ተቈጣጣሪ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አኪያልም የቤት አዛዥ፥ ኤልያቅም የቤት አዛዦች አለቃ ነበረ፥ የሳፋን ልጅ ኤልያፍም የቤተ ሰብ ሐላፊ፥ የአዶን ልጅ አዶኒራምም ግብር አስገባሪ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሒሳርም የቤት አዛዥ፥ የዓብዳም ልጅ አዶኒራም አስገባሪ ነበረ። |
ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ ኀላፊ የነበረውን አዶኒራምን ወደ እስራኤላውያን እንዲሄድ ላከው፤ እነርሱ ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህን ጊዜ ሮብዓም በፍጥነት ወደ ሠረገላው ገብቶ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ አመለጠ።
ሰሎሞን በመላው እስራኤል ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችን ሾመ፤ የእነርሱም ተግባር ከየግዛታቸው ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተሰብ ቀለብ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ማቅረብ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው።
ለሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ የኢየሩሳሌምን ቅጽር የሠሩለትና ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጐድጓዳ ስፍራ ሞልተው ያስተካከሉለት የጉልበት ሥራ ለመሥራት የሚገደዱ ሠራተኞች ነበሩ፤ እንዲሁም ሐጾር፥ መጊዶና ጌዜር ተብለው የሚጠሩ ከተሞችንም እንዲሠሩለት አደረገ።
ንጉሡም ሮብዓም አስገባሪውን አዶራምን ላከ፤ የእስራኤልም ልጆች በድንጋይ ወገሩት፥ ሞተም፤ ንጉሡም ሮብዓም ፈጥኖ ወደ ሠረገላው ወጣ ወደ ኢየሩሳሌምም ሸሸ።