1 ነገሥት 4:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች በምሳሌ እየመሰለ ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፥ ስለ ወፎች በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለ ዓሣዎችም አስተምሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሊባኖስ ዝግባ አንሥቶ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ስለ ዕፀዋት ተናግሯል፤ እንዲሁም ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በምድር ላይ ስለሚሳቡ ፍጥረታትና ስለ ዓሦችም ተናግሯል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች እየመሰለ ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፥ ስለ ወፎች በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለ ዓሣዎችም አስተምሮአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ዛፍም ከሊባኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው እስከ አሽክት ድረስ ይናገር ነበር፤ ደግሞም ስለ አውሬዎችና ስለ ወፎች ስለ ተንቀሳቃሾችና ስለ ዓሣዎች ይናገር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ዛፍም ከሊባኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው እስከ ሂሶጵ ድረስ ይናገር ነበር፤ ደግሞም ስለ አውሬዎችና ስለ ወፎች ሰለተንቀሳቃሾችና ስለ ዓሣዎች ይናገር ነበር። |
በመልክተኞችህ አማካይነት፥ በእግዚአብሔር ላይ ስድብህን ከምረሃል፤’ ‘በሠረገሎቼ ከፍተኛ ወደ ሆኑት ተራራዎች፤ ወደ ሊባኖስ ጫፍ ወጥቼአለሁ፤ ረጃጅሞቹን የሊባኖስ ዛፎችዋንና ምርጦች ዝግባ ቆርጬአለሁ፤ ወደ ዳርቻዋና ውብ ወደ ሆነው ጫካዋ ደርሼአለሁ፤’ ብለሃል።
ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፥ በዕቃ ውስጥ ባለው ደም ውስጥ ንከሩት፥ በዕቃውም ውስጥ ካለው ደም ጉበኖችንና ሁለቱን መቃኖች ቀቡ፤ ከእናንተም ማንም ሰው እስኪ ነጋ ድረስ ከቤቱ ደጅ አይውጣ።
ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።
የዝግባውን እንጨት፥ ሂሶጱንም፥ ቀዩንም ግምጃ፥ በሕይወትም ያለውን ወፍ ወስዶ በታረደው ወፍ ደምና በምንጩ ውኃ ውስጥ ይነክራቸዋል፥ ቤቱንም ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።
ንጹሕም ሰው ሂሶጱን ወስዶ በውኃው ውስጥ ይነክረዋል፤ በድንኳኑም፥ በዕቃውም ሁሉ፥ በዚያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ ዐፅሙንም ወይም የተገደለውን ወይም የሞተውን ወይም መቃብሩን በነካው ሰው ላይ ይረጨዋል፤
ወደፊትም ተዘርግቶ እንዳለው ሸለቆች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች፥ ጌታ እንደ ተከለው ዓልሙን በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል።
እያንዳንዱን የሕግ ትእዛዝ በሙሴ ለሕዝቡ ከተነገረ በኋላ የጥጆችን ደም ከውሃ፥ ከቀይ የበግ ጠጒርና ከሂሶጵ ጋር ወስዶ፥ በመጽሐፉና በሕዝቡ ላይ ረጨው፤