1 ነገሥት 21:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአውራጆቹም አለቆች ጉልማሶች አስቀድመው ወጡ፥ የአዴርም ልጅ መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም፦ “ሰዎች ከሰማርያ ወጥተዋል” ብለው ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቴስብያዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቲስቢያዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአውራጃዎቹም አለቆች ጐልማሶች አስቀድመው መጥተው ለሶርያ ንጉሥ ለወልደ አዴር፥ “እነሆ፥ ሰዎች ከሰማርያ መጡ” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአውራጆቹም አለቆች ጕልማሶች አስቀድመው ወጡ፤ ወልደ አዴርም መልእክተኞችን ላከ፥ እነርሱም፦ ሰዎች ከሰማርያ ወጥተዋል ብለው ነገሩት። |
ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ቴስቢያዊውን ኤልያስን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ተነሥተህ የሰማርያ ንጉሥ አካዝያስ የላካቸውን መልእክተኞች ለመገናኘት ውጣ፤ እንዲህም ብለህ ንገራቸው፤ ‘የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ የምትሄዱት፥ በእስራኤል ዘንድ አምላክ የለም ብላችሁ በማሰብ ነውን?’
ኤልሳዕም “ሰውየው ሊያነጋግርህ ከሠረገላው ላይ ሲወርድ እኔ በመንፈስ ከአንተ ጋር አልነበርኩምን? እነሆ አሁን ገንዘብና ልብስ፥ የወይራና የወይን ተክል ቦታ፥ በግና የቀንድ ከብት ወይም አገልጋዮችን ለመቀበል ጊዜው አይደለም!
በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቁጣውን ሊያመጣባቸው፥ እነሆ፥ ጌታ ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ያፈሰሰችውን ደም ትገልጣለች፥ የተገደሉትንም ከእንግዲህ ወዲህ አትሸሽግም።