ነገሥታት ለጦርነት በሚወጡበት በጸደይ ወራት ዳዊት ኢዮአብን ከአገልጋዮቹና ከመላው እስራኤል ጋር አዘመተው፤ እነርሱም አሞናውያንን አጠፉ፤ ራባ የተባለችውንም ከተማ ከበቡ፤ በዚህ ጊዜ ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።
1 ነገሥት 20:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም በተከታዩ የጸደይ ወቅት ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ በእስራኤል ላይ አደጋ ለመጣል ወደ አፌቅ ከተማ ገሠገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተከታዩም የጸደይ ወራት ቤን ሃዳድ ሶርያውያንን አሰባስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ አፌቅ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም በተከታዩ የጸደይ ወቅት ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ በእስራኤል ላይ አደጋ ለመጣል ወደ አፌቅ ከተማ ገሠገሠ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ያጠፋቸው አሞራውያን እንደ ሠሩት ሁሉ፥ ጣዖትን በመከተል እጅግ ርኩስ ነገርን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ያጠፋቸው አሞራዊያን እንደ ሠሩት ሁሉ፥ ጣዖታትን በመከተል እጅግ ርኩስ ነገር ሠራ። |
ነገሥታት ለጦርነት በሚወጡበት በጸደይ ወራት ዳዊት ኢዮአብን ከአገልጋዮቹና ከመላው እስራኤል ጋር አዘመተው፤ እነርሱም አሞናውያንን አጠፉ፤ ራባ የተባለችውንም ከተማ ከበቡ፤ በዚህ ጊዜ ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።
ከዚህ በኋላ ነቢዩ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ የሶርያ ንጉሥ በሚመጣው የጸደይ ወራት እንደገና አደጋ ስለሚጥልብህ “ተመልሰህ ሂድና ሠራዊትህን በማጠናከር አደራጅ፤ ጥንቃቄ የሞላበትንም የጦርነት ስልት አዘጋጅ” አለው።
ከዚህ በፊት የተደመሰሰውን የሚያኽል ብዙ ሠራዊትና እንዲሁም በቀድሞዎቹ ልክ ፈረሶችንና ሠረገሎችን አደራጅ፤ ከዚያም በኋላ እስራኤላውያንን በሜዳ ተዋግተን ድል እንነሣቸዋለን።” ንጉሥ ቤንሀዳድም በእነርሱ ምክር ተስማምቶ ለመፈጸም ወሰነ።
ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቁጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።
ኤልሳዕ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም “ፍላጻውን አስፈንጥር!” አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፥ “ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ።”
አሴርም በዓኮ፥ በሲዶን፥ በአሕላብ፥ በአክዚብ፥ በሒልባ፥ በኣፌቅና በረአብ የሚኖሩትን ሕዝብ በምድሪቱ ካሉት ከነዓናውያን ጋር አብረው ኖሩ።
የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤል ሁሉ ደረሰ። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ሊወጉ ወጡ፤ እነርሱ በአቤንኤዘር ሲሰፍሩ፥ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፈሩ።