1 ነገሥት 14:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ምክንያት እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ ከቤቱም ነጻም ሆነ ባርያ፥ ወንድ ልጅንም ሁሉ ከእስራኤል አጠፋለሁ፤ ፋንድያን አቃጥለው እንደሚጨርሱት የኢዮርብዓምን ቤት አወድማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ስለዚህ እኔም በኢዮርብዓም ቤት ላይ ጥፋትን አመጣለሁ፤ ባሪያም ይሁን ነጻ ዜጋ የኢዮርብዓምን ወንድ ልጅ ሁሉ ከእስራኤል አስወግዳለሁ፤ ኩበትም ዐመድ እስኪሆን ድረስ እንደሚቃጠል፣ እኔም የኢዮርብዓምን ቤት እንዲሁ አቃጥላለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ምክንያት እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ ከቤቱም ነጻም ሆነ ባሪያ፥ ወንድ ልጅን ሁሉ ከእስራኤል አጠፋለሁ፤ ፋንድያን አቃጥለው እንደሚጨርሱት የኢዮርብዓምን ቤት አወድማለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ መከራን አመጣለሁ፤ ኢዮርብዓምንም አጠፋዋለሁ፤ አጥር ተጠግቶ እስከሚሸን ወንድ ድረስ አላስቀርለትም፤ በእስራኤልም ላይ ይነግሥ ዘንድ አልተወውም፤ ሰው ገለባ እስኪያልቅ ድረስ እንደሚያነድድ በኢዮርብዓም ቤት ላይ እሳትን አነዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ መከራ አመጣለሁ፤ ከኢዮርብአምም በእስራኤል ዘንድ የታሰረውንና የተለቀቀውን ወንድ ሁሉ እቆርጣለሁ፤ ሰውም ፋንድያን እስኪጠፋ ድረስ እንደሚጠርግ እኔ የኢዮርብዓምን ቤት ፈጽሜ እጠርጋለሁ። |
ሰማርያንና የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ከነዘሮቹ እንደ ቀጣሁ ሁሉ ኢየሩሳሌምንም እቀጣለሁ፤ ሳሕን ከተወለወለ በኋላ ተደፍቶ እንደሚቀመጥ፥ እኔም ኢየሩሳሌምን ከኃጢአት አጸዳታለሁ።
ከሬሳውም የሚተርፈው እንደ ፍግ በዚያ ይበተናል፤ ስለዚህም ማንም እርሷነትዋን ለይቶ በማወቅ፦ ይህች ኤልዛቤል ናት፥ ሊል አይችልም’ ያለው ነው።”
አንተ ግን እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፤ በሰይፍም የተወጉት፥ ተገድለውም ወደ ጉድጓዱ ድንጋዮች የወረዱ ከድነውሃል፤ እንደተረገጠም ሬሳ ሆነሃል።
የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነዶአል፤ እጁን አንሥቶ መቶአቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ቁጣው ገና አልተመለሰም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
ለብዙ ሺህ ትውልድ ጽኑ ፍቅርን ታሳያለህ፥ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ፤ ታላቅና ኃያል አምላክ ሆይ! ስምህ የሠራዊት ጌታ ነው።
በወደዱአቸውና ባገለገሉአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፤ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።
በሰዎች ላይ ጭንቀትን አመጣለሁ፤ እንደ ዕውርም ይሄዳሉ፥ በጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርተዋልና፤ ደማቸው እንደ ትቢያ ይፈስሳል፥ ሥጋቸውም እንደ ጉድፍ ይጣላል።
እነሆ፥ ዘራችሁን እገሥጻለሁ፥ በፊታችሁ ላይ ፈርስን እበትናለሁ፥ ይህም ፈርስ ለበዓላችሁ መሥዋዕት ካመጣችኋቸው ነው፤ እናንተንም ከእርሱ ጋር ያነሳችኋል።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ።
ነገ ጠዋት የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ ወንድ እንኳ በሕይወት ባስቀር እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያድርግበት፥ ከዚህም የከፋ ይጨምርበት!”
ጉዳት እንዳላደርስብሽ የጠበቀኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው ጌታን! እንዲህ በቶሎ መጥተሽ ባታገኚኝ ኖሮ፥ እስኪ ነጋ ድረስ ለናባል አንድ ወንድ እንኳ ባልተረፈ ነበር።”