እንዲሁም ንጉሡ ካህኑን ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “አንተ ነቢይ አይደለህምን? ይሄውልህ አንተም ልጅህን አሒማአስን፥ የአብያታርን ልጅ ዮናታንን ይዘህ በሰላም ወደ ከተማዪቱ ተመለስ። አንተና አብያታር ሁለቱን ልጆቻችሁን ይዛችሁ ሂዱ።
1 ነገሥት 1:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ይህን ሲናገር የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ፥ አዶንያስም፦ “አንተ መልካም ሰው ነህና፥ መልካም ታወራልናለህና ግባ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ፣ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ደረሰ፤ አዶንያስም፣ “እንደ አንተ ያለ ታማኝ ሰው መልካም ዜና ሳይዝ አይመጣምና ግባ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ድንገት ደረሰ፤ አዶንያስም “እስቲ ና ግባ፤ አንተ ጥሩ ሰው ስለ ሆንክ መልካም ዜና ይዘህ ሳትመጣ አትቀርም” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ይህን ሲናገር የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ፤ አዶንያስም፥ “አንተ ኀያል ሰው ነህና፥ መልካምም ታወራልናለህና ግባ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ይህን ሲናገር የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ፤ አዶንያስም “አንተ መልካም ሰው ነህና፥ መልካም ታወራልናለህና ግባ፤” አለ። |
እንዲሁም ንጉሡ ካህኑን ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “አንተ ነቢይ አይደለህምን? ይሄውልህ አንተም ልጅህን አሒማአስን፥ የአብያታርን ልጅ ዮናታንን ይዘህ በሰላም ወደ ከተማዪቱ ተመለስ። አንተና አብያታር ሁለቱን ልጆቻችሁን ይዛችሁ ሂዱ።
እነሆ፥ የሳዶቅ ልጅ አሒማአስና የአብያታር ልጅ ዮናታን፥ ሁለቱ ወንዶች ልጆቻቸው እዚያው አብረዋቸው ይገኛሉ። የምትሰማትን ሁሉ በእነርሱ ላክልኝ።”
በዚህ ጊዜ ዮናታንና አሒማዓጽ ወደ ከተማዪቱ ከገቡ ስለሚታዩ በዔንሮጌል ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይ ወደዚያ እየሄደች በምትነግራቸው ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ ይህንኑ ወስደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር።
ጠባቂውም፥ “የመጀመሪያው ሰው ሩጫ የሳዶቅን ልጅ የአሒማዓጽን ሩጫ ይመስለኛል” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፤ ቢመጣም የምሥራች ይዞ ነው” አለ።
አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፥ ኢዮአብም የቀንደ መለከት ጽምፅ በሰማ ጊዜ፦ “ይህ በከተማ ውስጥ ያለ የሽብር ድምፅ ምንድነው?” አለ።
ኢዮራምም “ኢዩ ሆይ፥ አመጣጥህ በሰላም ነውን?” ሲል ጠየቀ። ኢዩም፦ “እናትህ ኤልዛቤል ባመጣችው አስማትና የጣዖት አምልኮ ውስጥ ተነክረን እስካለን ድረስ ምን ሰላም አለ?” ሲል መለሰለት።