1 ቆሮንቶስ 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስ ውሃ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን እግዚአብሔር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ተከልኩ፤ አጵሎስ ውሃ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን እግዚአብሔር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አሳደገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤ |
በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።
ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ ያሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።
በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ ነገር አዋቂ የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን ወረደ፤ እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ ነበረ።
እኔ የምለው፥ እያንዳንዳችሁ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤” “እኔስ የአጵሎስ ነኝ፤” “እኔ ግን የኬፋ ነኝ፤” “እኔስ የክርስቶስ ነኝ፤” ትላላችሁ።
ጳውሎስ ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉ የእናንተ ነው፤
ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ፥ በብዙም መረዳት እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ ስለ እናንተ ስንል በእናንተ መካከል ምን ዓይነት ሰዎች እንደ ነበርን እናንተው ታውቃላችሁ።