1 ቆሮንቶስ 15:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሰከነ ልቦናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና ይህንንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ሰከነ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኀጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና፤ ይህንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትም አትሥሩ፤ በእናንተ መካከል አንዳንዶች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉ። ይህንንም የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጽድቅ ትጉ፤ አትሳቱ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁት ሰዎች አሉና፤ ነገር ግን እንድታፍሩ ይህን እላችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጽድቅ ንቁ ኃጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና፤ አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። |
ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።
የመርከቡ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “እንዴት ትተኛለህ? ተነሥ አምላክህን ጥራ፥ ምናልባትም እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን ይሆናል” አለው።
ነገር ግን ይህ ዕውቀት በሁሉ ዘንድ አይገኝም፤ አንዳንዶች ግን ጣዖትን እስከ አሁን ድረስ ስለ ለመዱ፥ ለጣዖት የተሠዋ ነው፤ ብለው ይበላሉና፥ ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል።