1 ቆሮንቶስ 14:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልሳን የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርምና፤ ምስጢር የሆነውን በመንፈስ ስለሚናገር የሚረዳው የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልሳን የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርምና፤ ምስጢር የሆነውን በመንፈስ ስለሚናገር የሚረዳው የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ ምሥጢር የሆነውን ነገር በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ስለሚናገር የሚናገረውን ቃል የሚያውቀው የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቋንቋ የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው የሚናገር አይደለም። የሚናገረውን የሚሰማው የለምና፥ ነገር ግን በመንፈስ ምሥጢርን ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤ |
ከዚህም በኋላ ኤልያቄምና፥ ሼብና እንዲሁም ዮአሕ ይህን የጦር አዛዥ “ፍቹን ስለምናውቅ በሶርያ ቋንቋ እንድትነግረን እንለምንሃለን፤ በቅጽር ላይ ያሉት ሕዝብ ሁሉ በሚሰሙት በዕብራይስጥ ቋንቋ አትናገረን” አሉት።
ለሌላው ተአምራትን የማድረግ ኃይል ይሰጠዋል፤ ለሌላው ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱ መናፍስትን መለየት፥ ለሌላው በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለሌላውም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤
እግዚአብሔርም አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት የሚያደርጉትን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን፥ ሰዎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፥ አስተዳዳሪዎችንና በተለያዩ ልሳኖች የሚናገሩትን ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ሰይሟል።
ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝ፥ ምስጢርን ሁሉ ባውቅ፥ ዕውቀትን ሁሉ ብረዳ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
እንዲህማ ካልሆነ፥ በመንፈስ በምትባርክበት ጊዜ፥ አንተ የምትለውን የማያውቅ እንግዳ ሰው ካልተረዳ፥ እንዴት አድርጎ ለምስጋናህ፥ “አሜን” ሊል ይችላል?
ወንድሞች ሆይ፤ እንግዲህ ምን እንበል? በምትሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ መዝሙር አለው፤ ትምህርት አለው፤ መግለጥ አለው፤ በልሳን መናገር አለው፤ መተርጐም አለው። ይህ ሁሉ ግን ለማነጽ ይሁን።
ነገር ግን፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር ተሰውሮም የነበረውን እንናገራለን።
እንዲህም የምጋደለው ልባቸው እንዲጽናና፥ በፍቅርም በአንድነት እንዲተሳሰሩ፥ በፍጹም ማስተዋልም የሚገኘውን ባለጠግነት ሁሉ እንዲኖራቸው፥ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ ነው፤
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም፦ በሥጋ ተገለጠ፥ በመንፈስ ጸደቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፥ በመላው ዓለም ታመነ፥ በክብር ዐረገ፥ የሚል ነው።
ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ለመንፋት የተዘጋጀው መልአክ የመለከቱን ድምፁም በሚያሰማባቸው ቀኖች፥ የእግዚአብሔር ምሥጢር ለባርያዎቹ ለነቢያት የምሥራች በሰበከላቸው መሠረት ይፈጸማል፤” አለ።