1 ቆሮንቶስ 14:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍቅርን ተከታተሉ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን፥ በተለይም ትንቢት የመናገርን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍቅርን ተከታተሉ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን፣ በተለይም ትንቢት የመናገርን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ፍቅርን ተከታተሉ፤ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ይልቁንም ትንቢት የመናገር ስጦታን በብርቱ ፈልጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍቅርን ተከተሏት፤ ለመንፈሳዊ ስጦታ፥ ይልቁንም ትንቢት ለመናገር ተፎካከሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍቅርን ተከታተሉ፥ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ። |
ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝ፥ ምስጢርን ሁሉ ባውቅ፥ ዕውቀትን ሁሉ ብረዳ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በበጎም ሥራ ሁሉ በመትጋት፥ በመልካም ሥራዎችዋ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።
የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አንተ ግን ከእነዚህ ነገሮች ሽሽ፤ ጽድቅን፥ እግዚአብሔርን መምሰልን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ መጽናትን፥ የዋህነትን ግን ተከተል።
ከዚያ በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጦር ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ጊብዓ ትሄዳለህ። ወደ ከተማዪቱ እንደ ደረስክም የነቢያት ጉባኤ በበገና፥ በከበሮ፥ በዋሽንትና በመሰንቆ ታጅበው ትንቢት እየተናገሩ ከማምለኪያው ኰረብታ ላይ ሲወርዱ ታገኛቸዋለህ።