Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 12:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እንደ ተሰጠንም ጸጋ መጠን የተለያዩ ስጦታዎች አሉን፤ ትንቢት ከሆነ እንደ እምነት መጠን መናገር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እንደ ተሰጠን ጸጋ የተለያዩ ስጦታዎች አሉን፤ ለአንዱ የተሰጠው ስጦታ ትንቢት መናገር ከሆነ፣ እንደ እምነቱ መጠን ይናገር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ እግዚአብሔር በጸጋው የሰጠንን ልዩ ልዩ ስጦታ በሥራ ላይ እናውል፤ ስጦታችን የእግዚአብሔርን ቃል ማወጅ ከሆነ በእምነታችን መጠን የእግዚአብሔርን ቃል እናውጅ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠን ጸጋ መጠን ልዩ ልዩ ስጦታ አለን። ትን​ቢት የሚ​ና​ገር እንደ እም​ነቱ መጠን ይና​ገር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 12:6
31 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ እነሆ እኔ ነቢያትን፥ ጥበበኞችና ጻፎችን ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ ትሰቅላላችሁም፥ ከእነርሱም አንዳንዶቹን በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዱአቸዋላችሁ፤


ባለ ሁለት መክሊቱም ቀርቦ ‘ጌታ ሆይ! ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁ’ አለ።


ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፦ “ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም፤


በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርሲቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ።


ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኑአቸው።


“እግዚአብሔር ይላል ‘በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤


ለእርሱም ትንቢት የሚናገሩ አራት ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት።


የሚያጸናችሁን መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁ፤


እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ እንደሰጣችሁ እምነት መጠን፥ በረጋ አእምሮ አስቡ እንጂ ማሰብ ከሚገባችሁ በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ እናገራለሁና።


አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ የአካል ክፍሎችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል።


ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝ፥ ምስጢርን ሁሉ ባውቅ፥ ዕውቀትን ሁሉ ብረዳ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።


ፍቅርን ተከታተሉ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን፥ በተለይም ትንቢት የመናገርን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ።


ነገር ግን ሁሉም ትንቢት በመናገር ላይ እያሉ፥ እንግዳ ወይም የማያምን ሰው ቢገባ፥ በሚሰማው ቃል ሁሉ ይወቀሳል፤ በሚሰማው ቃል ሁሉ ይመረመራል፤


ሁለት ወይም ሦስት ነቢያት ይናገሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ የተነገረውን በጥንቃቄ ያመዛዝኑ።


አጵሎስ እንግዲህ ምንድነው? ጳውሎስስ ምንድነው? በእነርሱ በኩል ያመናችሁ፥ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደሰጣቸው፥ አገልጋዮች ናቸው፤


ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፤ አንዱ እንደዚህ ሌላውም እንደዚያ ዓይነት።


በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ ባለው ባለው መጠን ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ የሌላውን አይጠበቅበትም።


ይህ ምስጢር አሁን ለቅዱሳኑ ሐዋሪያትና ለነቢያት በመንፈስ እንደተገለጠው ባለፉት ትውልዶች ለነበሩ አልተገለጠም ነበር።


አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ የሰጠ እርሱ ነው፤


እንግዲህ በአእምሮ የበሰልን ሁላችን ይህን እናስብ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ፥ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል፤


ትንቢትን አትናቁ፤


ከሁሉ አስቀድማችሁ ይህን አስተውሉ፥ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos