1 ቆሮንቶስ 13:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ በከፊል የነበረው ይሻራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ በከፊል የነበረው ይሻራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ፍጹም የሆነው ነገር ሲመጣ ከፊል የሆነው ነገር ይሻራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ያ ተከፍሎ የነበረው ይሻራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል። |
ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላስል ነበር። ሙሉ ሰው በሆንኩ ጊዜ ግን የልጅነትን ጠባይ ትቻለሁ።
አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።
እኔ ግን አሁን ይህን አላገኘሁትም ወይም አሁን ፍጹም ለመሆን አልበቃሁም፤ ዳሩ ግን ክርስቶስ ኢየሱስ የራሱ አድርጎኛልና ይህን የራሴ ለማድረግ ወደ ፊት እሮጣለሁ።