1 ቆሮንቶስ 1:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም ሥጋ ለባሽ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረገው ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ። |
መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፤ ዘንግም ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኩራራ ነው።
ነገር ግን አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ ሥር እንዲሆን፤ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሚናገር እናውቃለን፤
አንተን እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልከውስ ምን አለህ? እንግዲህ የተቀበልክ ከሆንክ፥ እንዳልተቀበልክ የምትመካው ስለ ምንድነው?