1 ዜና መዋዕል 9:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚቅሎትም ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት በሚገኝ ስፍራ ይቀመጡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚቅሎት ሺሜዓን ወለደ፤ እነርሱም ደግሞ ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋራ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚቅሎት የሺምዓም አባት ነው እነርሱም በሌሎቹ በወንድሞቻቸው አቅራቢያ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሜቅሎትም ሳምአን ወለደ፤ እነርሱም ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው መካከል ይቀመጡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚቅሎትም ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ይቀመጡ ነበር። |