La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 9:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዕቃውም በቍጥር፥ ይገባና ይወጣ ነበርና ከእነዚህ እያንዳንዱ በመገልገያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ይቈጥሩ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሌሎቹ ሌዋውያን በአምልኮ ጊዜ መገልገያ ለሆኑ ንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች ነበሩ፤ በአገልግሎት ላይ በሚውሉበት ጊዜ እየቈጠሩ አውጥተው፥ አገልግሎታቸው ሲያበቃም እየቈጠሩ መልሰው ያስቀምጡአቸው ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዕቃ​ው​ንም በቍ​ጥር ያገ​ቡና ያወጡ ነበ​ርና ከእ​ነ​ዚህ አን​ዳ​ን​ዶቹ በማ​ገ​ል​ገ​ያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዕቃውም በቍር ይገባና ይወጣ ነበርና ከእነዚህ አንዳንዱ በማገልገያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 9:28
9 Referencias Cruzadas  

ከሌዋውያን አኪያ በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅዱሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሾሞ ነበር።


የእግዚአብሔርንም ቤት የሚጠብቁ፥ ጥዋት ጥዋትም ደጆቹን የሚከፍቱ እነርሱ ነበሩና በዚያ ያድሩ ነበር።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ በመቅደሱ ዕቃ ሁሉ በመልካሙም ዱቄት፥ በወይን ጠጁም፥ በዘይቱም፥ በዕጣኑም፥ በሽቶውም ላይ ሹሞች ነበሩ።


በዚያን ቀን በይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቁርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ።


በመቅደስም ውስጥ የሚገለገሉባቸውን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡአቸው፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑአቸው፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉአቸው።