1 ዜና መዋዕል 6:76 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ሐሞንና መሰማሪያዋ፥ ቂርያታይምና መሰምርያዋ ተሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ ሐሞንንና፣ ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንፍታሌም ግዛት በገሊላ ምድር የምትገኘው ቄዴሽ፥ ሐሞንና ቂርያታይም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ሐሞንና መሰማሪያዋ፥ ቄርያታይምና መሰማሪያዋ ተሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማርያዋ፥ ሐሞንና መሰማርያዋ፥ ቂርያታይምና መሰማርያዋ ተሰጡ። |
በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት-አርባቅን ለዩ።
ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞት-ዶንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
ዲቦራ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባራቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺህ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤