1 ዜና መዋዕል 6:71 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጎላንና መሰማሪያዋ፥ አስታሮትና መሰማሪያዋ ተሰጣቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌርሶናውያን ከዚህ የሚከተሉትን ከተሞች ወሰዱ፤ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጌርሾን ጐሣ ቤተሰቦች የሚከተሉት ከተሞች በዙሪያቸው ከሚገኙት የግጦሽ ቦታዎች ጋር ተመድበውላቸው ነበር፦ በምሥራቅ በኩል ካለው ከምናሴ ግዛት በባሳን ያለው ጎላንና ዐስታሮት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጋውሎንና መሰማሪያዋ፥ አስታሮትና መሰማሪያዋ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኵሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጎላንና መሰማርያዋ፥ አስታሮትና መሰማርያዋ፤ |
ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቤጼር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።
የገለዓድም እኩሌታ፥ በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበረ። እነዚህም ለማኪር ልጆች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ድርሻቸው ሆነ።
በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ።
ለሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነቸውን ጎላንንና መሰማሪያዋን፥ በኤሽትራንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።
በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።