1 ዜና መዋዕል 6:57 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአሮንም ልጆች እነዚህን የመማፀኛ ከተሞች ሰጡ፤ እርሱም፦ ኬብሮን፥ ልብናና መሰማሪያዋ፥ ደግሞ የቲር፥ ኤሽትሞዓና መሰማሪያዋ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአሮን ዘሮች የመማፀኛ ከተሞች የሆኑትን ኬብሮንን፣ ልብናን፣ የቲርን፣ ኤሽትሞዓን፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአሮን ልጆች የተመደቡ ከተሞች፥ የመማጠኛ ከተማ የሆነችው ኬብሮን፥ ያቲር፥ ሊብና፥ ኤሽተሞዓ፥ ሒሌን፥ ደቢር፥ ዐሻንና ቤትሼሜሽ ሲሆኑ የግጦሽ ቦታዎቻቸውንም ይጨምራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰማርያዋን፥ ሴልናንና መሰማሪያዋን፤ ኤስትሞዓንና መሰማሪያዋን ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰምርያዋን፥ ደግሞ የቲርን፥ ኤሽትሞዓንና መሰማርያዋን፥ |