ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለባርያህ፦ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ አልማልህልኝምን? ስለ ምንስ አዶንያስ ይነግሣል? በዪው።
1 ዜና መዋዕል 28:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በጌታ መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ሰጥቶኛል፤ ከወንዶቹ ልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ እንዲነግሥ ደግሞ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእኔም ብዙ ወንዶች ልጆችን ሰጠኝ፤ ነገር ግን የሚቀጥለው የእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ የመረጠው ልጄን ሰሎሞንን ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል። |
ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለባርያህ፦ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ አልማልህልኝምን? ስለ ምንስ አዶንያስ ይነግሣል? በዪው።
በእውነት ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በእኔም ፋንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል ብዬ በእስራኤል አምላክ በጌታ እንደ ማልሁልሽ፥ እንዲሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ” ብሎ ማለ።
በኋላውም ተከትላችሁ ውጡ፥ እርሱም መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ፥ በእኔም ፋንታ ይንገሥ፥ በእስራኤልና በይሁዳም ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ አዝዣለሁ።”
አዶንያስም እንዲህ አላት፦ “ንጉሥ መሆን የሚገባኝ እኔ እንደ ነበርኩና ይህንንም በእስራኤል ምድር የሚኖር ሁሉ በተስፋ ይጠባበቅ እንደ ነበር አንቺ ራስሽ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ጉዳዩ ከጌታ ስለ ተወሰነ ለእኔ መሰጠት የሚገባው መንግሥት ተላልፎ ለወንድሜ ሆኖአል።
“እነሆ ጌታ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቆአል፤ ስለዚህም እኔ በአባቴ ቦታ ተተክቼ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀመጥኩ፤ ጌታም ቃል እንደገባው፥ ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ለስሙ ቤት ሠራሁ።
ንጉሡም ዳዊት ለጉባኤው ሁሉ እንዲህ አለ፦ “በብቸኛነት እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ብላቴና ለጋ ነው፤ ሕንጻው ግን ለጌታ ለአምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው።
በአምላክህ በጌታ ፊት ንጉሥ እንድትሆን በዙፋኑ ላይ ሊያስቀምጥህ የወደደህ አምላክህ ጌታ ብሩክ ይሁን፤ አምላክህ እስራኤልን ለዘለዓለም ሊያጸናቸው ወድዶአቸዋልና ስለዚህ ፍርድና ጽድቅ እንድታደርግ በእነርሱ ላይ አነገሠህ።”
ጌታ እግዚአብሔር የሚመርጠውን ንጉሥ በላይህ ልታነግሥ ትችላለህ፤ የምታነግሠውም ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንጂ፥ እስራኤላዊ ወንድምህ ያልሆነውን ባዕድ በላይህ አታንግሥ።