1 ዜና መዋዕል 26:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጦርነትም ከተገኘው ምርኮ የጌታን ቤት ለመሥራት ስጦታ ቀድሰው ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጦርነት ከተገኘውም ምርኮ ከፊሉን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ማደሻ እንዲሆን ቀደሱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ኀላፊዎችም በጦርነት ጊዜ ከተገኘው ምርኮ ጥቂቱን ወስደው ለቤተ መቅደሱ ሥራ የተለየ እንዲሆን ያደርጉ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሕንጻ ወደ ኋላ እንዳይል ዳዊት ከየሀገሩ በማረካቸውና በሰበሰባቸው በቀደሳቸውም ላይ የተሾሙ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰልፍም ከተገኘው ምርኮ የእግዚአብሔርን ቤት ለማበጀት ቀደሱ። |
ንጉሡም ዳዊት ከአሕዛብ ሁሉ ከኤዶምና ከሞዓብ ከአሞንም ልጆች ከፍልስጥኤማውያንም ከአማሌቅም ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ደግሞ ለጌታ ቀደሰ።
ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች የሠራዊቱም አዛዦች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሾመው ነበር።
ባለ ራእዩም ሳሙኤል፥ የቂስም ልጅ ሳኦል፥ የኔርም ልጅ አበኔር፥ የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ የቀደሱት ንዋየ ቅድሳት ሁሉ ከሰሎሚትና ከወንድሞቹ ሥልጣን በታች ነበረ።
እንዲሁም ሰሎሞን ለጌታ ቤት የሚሠራውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን የብርና የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰሎሞን አምጥቶ በጌታ ቤት ውስጥ በነበረው ግምጃ ቤት አኖረው።