1 ዜና መዋዕል 24:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሙሲም ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ዔደር፥ ኢያሪሙት ነበሩ። እነዚህም እንደ አባቶቻቸው ቤቶች የሌዋውያን ልጆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ለኢያሪሙት። እነዚህ እንግዲህ እንደየቤተ ሰባቸው የተቈጠሩ ሌዋውያን ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሙሺም ልጆች፥ ማሕሊ፥ ዔዴርና ያሪሞት ነበሩ። እንግዲህ እነዚህ ሁሉ የሌዊ ዘር ቤተሰቦች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐሙሲ ልጆች፤ ሞዓሊ፥ ኤዳር፥ ኢያሪሞት። እነዚህ እንደ አባቶቻቸው ቤቶች የሌዋውያን ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሙሲም ልጆች ሞሖሊ፥ ዔደር፥ ኢያሪሙት። እነዚህም እንደ አባቶቻቸው ቤቶች የሌዋውያን ልጆች ነበሩ። |
እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላቁም እንደ ታናሹ፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።