La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 23:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲሁም በየጥዋቱና በየማታው ቆመው ጌታን በማመስገንና በማክበር፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በየዕለቱም እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለመወደስ ጧት ጧት ይቆሙ ነበር፤ ይህንም ማታ ማታ

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዘወትር ጠዋትና ማታ፥ እንዲሁም ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ የሚቀርበው ነገር በሚቃጠልበት በየሰንበቱ፥ በየወሩ መባቻና በሌሎችም በዓላት እግዚአብሔርን ማመስገንና ማክበር የእነርሱ ተግባር ነበር፤ በየጊዜው ይህን አገልግሎት የሚፈጽሙ ሌዋውያን ቊጥራቸው ምን ያኽል መሆን እንደሚገባው ደንቦች ነበሩ፤ ሌዋውያን እግዚአብሔርን ለማምለክ በሚደረገው ሥነ ሥርዓት ለሁልጊዜ ተመድበዋል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታው ቆመው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገ​ንና ለማ​ክ​በር፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሥራቸውም በየጥዋቱና በየማታው ቆመው እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማክበር፥

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 23:30
19 Referencias Cruzadas  

ደግሞም የተቀደሰ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም፥ ለእህል ቁርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በመለክያ ሁሉ ያገልግሉ ነበር።


በየሰንበታቱም በየመባቻዎቹም በየበዓላቱም እንደ ሥርዓቱ ቍጥር በጌታ ፊት ዘወትር ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ በማቅረብ፥


አራቱ ሺህም የደጁ ጠባቂዎች ነበሩ፤ አራቱ ሺህም ለምስጋና በተሰሩት በዜማ ዕቃዎች ጌታን ያመሰግኑ ነበር።


የእግዚአብሔርንም ቤት የሚጠብቁ፥ ጥዋት ጥዋትም ደጆቹን የሚከፍቱ እነርሱ ነበሩና በዚያ ያድሩ ነበር።


ከሌዋውያንም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን እነዚህ ናቸው፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረና ያለ ሌላ ሥራ በየእልፍኛቸው ይቀመጡ ነበር።


ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው አቆመ፤ በጌታ ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ እንዲያገለግሉ፥ እንዲያመሰግኑም ክብርም እንዲሰጡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን አቆመ።


በዙፋኑም ፊት፥ በአራቱም ሕያዋን ፍጡራንና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያንን ቅኔ ማንም ሊማረው አልቻለም።