አለቃው ኢኢት ነበረ፤ ሁለተኛው ዚዛ ነበረ፤ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ስለዚህ እንደ አንድ አባት ቤት ሆነው ተቈጠሩ።
1 ዜና መዋዕል 23:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀነዓት ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል አራት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀዓት ወንዶች ልጆች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፤ በአጠቃላይ አራት ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀዓትም ዓምራም፥ ዩጺሃር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀዓት ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፦ ኬብሮን፥ ዑዝኤል አራት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀነዓት ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል አራት ነበሩ። |
አለቃው ኢኢት ነበረ፤ ሁለተኛው ዚዛ ነበረ፤ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ስለዚህ እንደ አንድ አባት ቤት ሆነው ተቈጠሩ።
የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ከሁሉ በላይ የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፥ እርሱና ልጆቹ፥ ለዘለዓለም በጌታ ፊት እንዲያጥኑና እንዲያገለግሉ፥ በስሙም ለዘለዓለም እንዲባርኩ ተለይተው ነበር።
እነዚህ የሌዊ ወገኖች ናቸው፤ የሊብናውያን ወገን፥ የኬብሮናውያን ወገን፥ የሞሖላውያን ወገን፥ የሙሳውያን ወገን፥ የቆሬያውያን ወገን። ቀዓትም እንበረምን ወለደ።
በቀዓት ውስጥም የእንበረማውያን ወገን፥ የይስዓራውያንም ወገን፥ የኬብሮናውያንም ወገን፥ የዑዝኤላውያንም ወገን ይካተቱ ነበር፤ የቀዓታውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው።