1 ዜና መዋዕል 22:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለ፦ “ልጄ ሆይ! እኔ ለአምላኬ ለጌታ ቤት እንድሠራ በልቤ አስቤ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፤ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ለመሥራት በልቤ ዐስብ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ክብር ቤተ መቅደስ ለመሥራት በልቤ አስቤ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እኔ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ በልቤ አስቤ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለ “ልጄ ሆይ! እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ቤት እሠራ ዘንድ በልቤ አስቤ ነበር። |
“በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ።
አሁንም አምላካችሁን ጌታን ለመሻት ልባችሁንና ነፍሳችሁን ለእርሱ አሳልፋችሁ ስጡ፤ ለጌታም ስም ወደሚሠራው ቤት የጌታን የቃል ኪዳኑን ታቦትና የእግዚአብሔርን ንዋየ ቅድሳት ለማምጣት ተነሥታችሁ የጌታን የእግዚአብሔርን መቅደስ ሥሩ።”
ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ፥ ለመቅደሱ ካዘጋጀሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ።
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በጌታ ፊት መዓዛው ያማረውን ሽቶ ዕጣን ለማጠን፥ የተቀደሰውንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም በመባቻዎቹም በአምላካችንም በጌታ በዓላት ለማቅረብ ለአምላኬ ለጌታ ስም ቤት ልሠራለትና ልቀድስለት አሰብሁ።
ይህን ሊለውጡ፥ በኢየሩሳሌም ያለውንም የእግዚአብሔርን ቤት ሊያፈርሱ እጃቸውን የሚዘረጉትን ነገሥታትና አሕዛብ ሁሉ፥ ስሙን በዚያ ያኖረው አምላክ ያጥፋው። እኔ ዳርዮስ ይህን አዝዣለሁ፥ በትጋት ይፈጸም።”
ጌታ አምላካችሁም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ እንዲሁም ለጌታ የተሳላችሁትን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ።
ስሙን ለማኖር ጌታ እግዚአብሔር የመረጠው ስፍራ ከአንተ እጅግ የራቀ ከሆነ፥ ባዘዝሁህ መሠረት ከቀንድ ከብትህ፥ ከበግና ከፍየል መንጋህ እንስሳት ማረድ ትችላለህ፤ በከተሞችህ ውስጥ የምትፈልገውን ያህል መብላት ትችላለህ።