1 ዜና መዋዕል 21:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ለዳዊት ባለ ራእይ ለጋድ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም የዳዊት ባለራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የዳዊት ነቢይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለነቢዩ ለጋድ እንዲህ አለው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርንም ለዳዊት ባለ ራዕይ ለጋድ |
“ሂድ፥ ለዳዊት፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሦስቱን ነገሮች በፊትህ አኖራለሁ፤ በአንተ ላይ እንዳደርግብህ ከእነርሱ አንዱን ምረጥ’ ብለህ ንገረው” ብሎ ተናገረው።
እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡ ባለ ራእይ የሆነው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው።
የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።
ይህንም ትእዛዝ ጌታ በነቢያቱ እጅ አዝዞአልና እንደ ዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን ትእዛዝ፥ ጸናጽልና በገና መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንን በጌታ ቤት አቆመ።
ይሁን እንጂ ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፥ “በዐምባው ውስጥ አትቆይ፤ ሂድና ወደ ይሁዳ ምድር ግባ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ።
ቀደም ሲል በእስራኤል ዘንድ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፥ “ኑ፥ ወደ ባለ ራእዩ እንሂድ” ይል ነበር፤ ዛሬ ነቢይ የሚባለው በዚያ ጊዜ ባለ ራእይ ይባል ነበርና።