Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 29:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ይህንም ትእዛዝ ጌታ በነቢያቱ እጅ አዝዞአልና እንደ ዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን ትእዛዝ፥ ጸናጽልና በገና መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንን በጌታ ቤት አቆመ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ንጉሥ ሕዝቅያስም በዳዊት፣ በንጉሡ ባለራእይ በጋድና በነቢዩ በናታን በተሰጠው መመሪያ መሠረት ሌዋውያኑን ጸናጽል፣ በገናና መሰንቆ አስይዞ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መደባቸው፤ ይህም በነቢያት አማካይነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ትእዛዝ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ንጉሥ ሕዝቅያስ እግዚአብሔር በነቢዩ ጋድና በነቢዩ ናታን አማካይነት ለንጉሥ ዳዊት የሰጠውንና ዳዊትም ተግባራዊ ያደረገውን ትእዛዝ በመከተል በበገና፥ በጸናጽልና በመሰንቆ የሠለጠኑ ሌዋውያንን በቤተ መቅደሱ ውስጥ መደበ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ይህ​ንም ትእ​ዛዝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያቱ እጅ አዝ​ዞ​አ​ልና እንደ ዳዊ​ትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢ​ዩም እንደ ናታን ትእ​ዛዝ፥ ጸና​ጽ​ልና በገና፥ መሰ​ን​ቆም አስ​ይዞ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቆመ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ይህንም ትእዛዝ እግዚአብሔር በነቢያቱ እጅ አዝዞአልና እንደ ዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን ትእዛዝ፥ ጸናጽልና በገና መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንን በእግዚአብሔር ቤት አቆመ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 29:25
19 Referencias Cruzadas  

በማግስቱ ጠዋት ዳዊት ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ የጌታ ቃል የዳዊት ባለ ራእይ ወደ ሆነው ወደ ነቢዩ ወደ ጋድ መጣ፤


ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ከፍ አድርገው ለማሰማት መለከትና ጸናጽል ለእግዚአብሔርም መዝሙራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤዶታምም ልጆች ጠባቂዎች ነበሩ።


ጌታም ለዳዊት ባለ ራእይ ለጋድ፦


አራቱ ሺህም የደጁ ጠባቂዎች ነበሩ፤ አራቱ ሺህም ለምስጋና በተሰሩት በዜማ ዕቃዎች ጌታን ያመሰግኑ ነበር።


ደግሞም ለጌታ ቤት አደባባዮችና በዙሪያው ለሚሆኑ ጓዳዎች፥ ለእግዚአብሔርም ቤት ለሚሆኑ ቤተ መዛግብት፥ ለንዋየ ቅድሳቱም ለሚሆኑ ቤተ መዛግብት በመንፈሱ ያሰበውን ንድፈ ሐሳብ ሁሉ ሰጠው።


ዳዊትም፦ “የሥራውን ሁሉ ንድፈ ሐሳብ እንዳውቅ ይህ ሁሉ በጌታ እጅ ተጽፎ መጣልኝ” አለ።


የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።


ከሌዋውያንም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን እነዚህ ናቸው፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረና ያለ ሌላ ሥራ በየእልፍኛቸው ይቀመጡ ነበር።


ደግሞም አንድ ልብ እንዲሰጣቸው፥ በጌታም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የሹማምንቱን ትእዛዝ እንዲያደርጉ የጌታ እጅ በይሁዳ ላይ ነበረ።


በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ልጆች የቂጣውን በዓል በታላቅ ደስታ ሰባት ቀን አከበሩ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በዜማ ዕቃ ለጌታ እየዘመሩ ዕለት ዕለት ጌታን ያመሰግኑ ነበር።


የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሣፍም እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደነበረው እንደ ኤዶታም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ የደጁም ጠባቂዎች በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው እንዲርቁ አያስፈልጋቸውም ነበር።


የጌታም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዓት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዓታቸው እንዲያመሰግኑ፥ በካህናቱም ፊት እንዲያገለግሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ ጠባቂዎችንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።


የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ምረቃውን በደስታ፥ በምስጋና፥ በመዝሙር፥ በጸናጽል፥ በበገናና በክራር ለማክበር ሌዋውያኑን ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በየሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ፈለጉ።


ይሁን እንጂ ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፥ “በዐምባው ውስጥ አትቆይ፤ ሂድና ወደ ይሁዳ ምድር ግባ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos