1 ዜና መዋዕል 21:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ወደ ኦርና በመጣ ጊዜ ኦርና ቀና ብሎ ተመለከተ ዳዊትንም አየ፤ ከአውድማውም ወጥቶ ዳዊትን እጅ ሊነሣ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ወደ እርሱ እየቀረበ መጣ፤ ኦርናም ቀና ብሎ ሲመለከት፣ ዳዊትን አየው፤ ከዐውድማውም ወጥቶ መሬት ላይ ለጥ ብሎ በመደፋት ለዳዊት እጅ ነሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦርናም ዳዊት ወደ እነርሱ እየቀረበ መምጣቱን ባየ ጊዜ ከአውድማው ወጥቶ ወደ መሬት ለጥ በማለት እጅ ነሣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ኦርና መጣ፤ ኦርናም ከአውድማው ወጥቶ ዳዊትን ተቀበለው። በምድርም ላይ ወድቆ ሰገደለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ ኦርና በመጣ ጊዜ ኦርና ተመልክቶ ዳዊትን አየ፤ ከአውድማውም ወጥቶ ዳዊትን እጅ ሊነሣ በምድር ላይ ተደፋ። |
ዳዊትም ኦርናን፦ “በላዩ ለጌታ መሠዊያ እንድሠራ ይህን የአውድማ ስፍራ ስጠኝ፤ ሙሉ ዋጋ ልክፈልና ስጠኝ፤ መቅሰፍቱም ከሕዝቡ ይከለከላል” አለው።
የእሳቱ ነበልባል ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ፥ የጌታ መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ዐረገ። ማኑሄና ሚስቱ ይህን ሲመለከቱ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።