Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 13:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የእሳቱ ነበልባል ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ፥ የጌታ መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ዐረገ። ማኑሄና ሚስቱ ይህን ሲመለከቱ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ይኸውም የእሳቱ ነበልባል ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ፣ የእግዚአብሔር መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ዐረገ። ማኑሄና ሚስቱ ይህን ሲመለከቱ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ነበልባሉ ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ ማኑሄና ሚስቱ እየተመለከቱ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ሆኖ ወደ ላይ ወጣ፤ እነርሱም በግንባራቸው በመሬት ላይ ተደፉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ነበ​ል​ባ​ሉም ከመ​ሠ​ዊ​ያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ ነበ​ል​ባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ተመ​ለ​ከቱ፤ በም​ድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ፥ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፥ በምድርም በግምባራቸው ተደፉ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 13:20
14 Referencias Cruzadas  

አብራምም በግምባሩ ወደቀ፥ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “እነሆ፥ ቃል ኪዳኔ ከአንተ ጋር ነው፥


እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።


ዳዊትም ዐይኖቹን አነሣ፤ የጌታ መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትም ሽማግሌዎችም ማቅ ለብሰው በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።


ዳዊትም ወደ ኦርና በመጣ ጊዜ ኦርና ቀና ብሎ ተመለከተ ዳዊትንም አየ፤ ከአውድማውም ወጥቶ ዳዊትን እጅ ሊነሣ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደ።


ዳዊትም በዚያ ለጌታ መሠዊያ ሠራ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት አቀረበ፥ ጌታንም ጠራ፤ ጌታም ከሰማይ የሚቃጠለው መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት።


ለሚወደው ለያዕቆብ ኩራት የሆነችውን ርስታችንን እርሱ ይመርጥልናል።


ከራሳቸው በላይ ካለው ሰማይ በላይ ዙፋን የሚመስል ነበረ፥ እርሱም የሰንፔር ድንጋይ ይመስል ነበር፥ ዙፋን በሚመስለው፥ በላዩ ላይም ሰው የሚመስል ነበረ።


በዝናብ ቀን በደመና ውስጥ እንዳለ ቀስተ ደመና የሚመስል፥ በዙሪያው የከበበው ብርሃንም እንዲሁ ይመስል ነበር። ይህም የጌታ ክብር መልክ አምሳያ ነበር። ባየሁትም ጊዜ በግምባሬ ተደፋሁ፥ የሚናገር ድምፅም ሰማሁ።


እሳትም ከጌታ ዘንድ ወጣ፥ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እልል አሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ሰገዱ።


ደቀመዛሙርቱ ይህንን ሰምተው በፊታቸው ወደቁ፤ እጅግም ፈርተው ነበር።


እርሱም የክብሩ ጸዳልና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኀጢአታችንን ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤


ጌዴዎን ወደ ቤቱ ሄደ፤ የፍየል ጠቦትም ዐረደ፤ አንድ ኢፍ መስፈሪያ ዱቄት ወስዶ እርሾ ያልገባበት ቂጣ ጋገረ። ሥጋውን በቅርጫት፥ መረቁን በምንቸት ይዞ በመምጣት በባሉጥ ሥር ለተቀመጠው አቀረበለት።


መልአኩም በያዘው በትር ጫፍ ሥጋውንና ቂጣውን ነካ፤ ከዐለቱም እሳት ወጥቶ ሥጋውንና ቂጣውን በላ፤ ከዚያም የጌታ መልአክ ተሰወረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos