1 ዜና መዋዕል 16:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር ሁሉ በፊቱ ትናወጥ፤ ዓለሙም ፍጹም እንዳይናወጥ በጽኑ ይታነጻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር ሁሉ በፊቱ ትንቀጥቀጥ፤ ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥምም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድር ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጡ! ምድር በጽኑ ስለ ተመሠረተች አትናወጥም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጣለች፤ ዓለምንም እንዳትነዋወጥ አጸናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ፤ ዓለሙም እንዳይናወጥ ጸንቶአል። |
“ጌታ እንዲህ ይላል፦ በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፥ በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ፤ እጠብቅሃለሁ፥ ምድርንም እንድታቀና፥ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች እንድታወርስ፥
ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”