Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 16:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል፦ “ጌታ ነግሷል” ይበሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል፤ “እግዚአብሔር ነገሠ!” ይበሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ሰማይና ምድር ደስ ይበላቸው! ሕዝቦች ሁሉ “እግዚአብሔር ንጉሥ ነው” ይበሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፥ ምድ​ርም ሐሤ​ትን ታድ​ርግ፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ” በሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል “እግዚአብሔር ነገሠ፤” በሉ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 16:31
19 Referencias Cruzadas  

ምድር ሁሉ በፊቱ ትናወጥ፤ ዓለሙም ፍጹም እንዳይናወጥ በጽኑ ይታነጻል።


የዳዊት የምስጋና መዝሙር። አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም እባርካለሁ።


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።


እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፥ በጥበብ ዘምሩ።


ዘርህን ለዘለዓለም አዘጋጃለሁ፥ ዙፋንህንም ለልጅ ልጅ እመሠርታለሁ።


በአሕዛብ መካከል፦ “ጌታ ነገሠ” በሉ። እንዳይናወጥም ዓለሙን እርሱ አጸናው፥ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


ጌታ ነገሠ፥ ምድር ሐሤትን ታድርግ፥ ብዙ ደሴቶችም ደስ ይበላቸው።


ምድር ሁሉ ሆይ፥ ለጌታ እልል በሉ፥ በደስታ ፈንድቁ፥ ዘምሩም።


ጌታ ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፥ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።


ጌታ ፈራጃችን ነው፥ ጌታ ሕግን ሰጪያችን ነው፥ ጌታ ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።


ሰማያት ሆይ፥ ጌታ አድርጎታልና ዘምሩ፤ ጌታ ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፥ ጩኽ፤ እናንተም ተራሮች አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፥ እልል በሉ።


ጌታ ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ለችግረኞቹም ራርቶአልና ሰማያት ሆይ፥ ዘምሩ፥ ምድር ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ተራሮችም ሆይ፥ እልል በሉ።


ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’


እንዲሁ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ ምክንያት በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።”


መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ደስታ የሚሆን የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤


የብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ የብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ የብርቱም ነጐድጓድም ድምፅ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos