Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 16:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ምድር ሁሉ በፊቱ ትንቀጥቀጥ፤ ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥምም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ምድር ሁሉ በፊቱ ትናወጥ፤ ዓለሙም ፍጹም እንዳይናወጥ በጽኑ ይታነጻል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የምድር ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጡ! ምድር በጽኑ ስለ ተመሠረተች አትናወጥም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ምድር ሁሉ በፊቱ ትነ​ዋ​ወ​ጣ​ለች፤ ዓለ​ም​ንም እን​ዳ​ት​ነ​ዋ​ወጥ አጸ​ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ፤ ዓለሙም እንዳይናወጥ ጸንቶአል።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 16:30
15 Referencias Cruzadas  

ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ።


እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፤ ውዳሴውም ብዙ ነው፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል።


ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤ መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤ በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር ስገዱ።


ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል፤ “እግዚአብሔር ነገሠ!” ይበሉ።


እርሱ ተናግሯልና ሆኑ፤ አዝዟልና ጸኑም።


አንተ ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፤ ምድርም ፈርታ ጸጥ አለች፤


እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም።


በተቀደሰ ውበት ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ ምድር ሁሉ፤ በፊቱ ተንቀጥቀጡ።


እግዚአብሔር ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን ተቀምጧል፤ ምድር ትናወጥ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በተወደደ ጊዜ እመልስልሃለሁ፤ በድነት ቀን እረዳሃለሁ። ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንድትሆን፣ ምድሪቱን እንደ ገና እንድትሠራት፣ ጠፍ የሆኑትን ርስቶች ለየባለቤታቸው እንድትመልስ፣ እጠብቅሃለሁ፤ እሠራሃለሁም፤


እርሱ ግን ምድርን በኀይሉ ፈጠረ፤ ዓለምን በጥበቡ መሠረተ፤ ሰማያትንም በማስተዋሉ ዘረጋ።


እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በርሱ ነው።


እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዟል። የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።


ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፤ “የዓለም መንግሥት፣ የጌታችንና የርሱ ክርስቶስ መንግሥት ሆነች፤ እርሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos