La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 11:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሁለተኛውም ተራ በሆኑት በሦስቱ መካከል የከበረ ነበረ፥ አለቃቸውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ ደረጃ አልደረሰም ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሦስቱ አንዱ ሆኖ ባይቈጠርም እንኳ፣ ዕጥፍ ክብር አገኘ፤ አዛዣቸውም ሆነ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሦስቱ ጀግኖች መካከል እንደ አንዱ ባይቈጠርም በሠራው ጀብዱ ከእነርሱ ይበልጥ እጥፍ ድርብ ክብር በማግኘቱ የእነርሱ አለቃ ለመሆን በቃ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ተራ በሆ​ኑት በሦ​ስቱ መካ​ከል የከ​በረ ነበረ፥ አለ​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ፊተ​ኞቹ ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሁለተኛውም ተራ በሆኑት በሦስቱ መካከል የከበረ ነበረ፤ አለቃቸውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ አልደረሰም

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 11:21
6 Referencias Cruzadas  

የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ኀያላን አለቃ ነበረ። በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን ሰብቆ የገደላቸውና ስሙም ከሦስቱ ኀያላን ጋር የሚጠራ ነበረ።


የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ጦሩንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፥ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ።


በቀብስኤልም የነበረው፥ ታላቅ ሥራ ያደረገው የጽኑዕ ሰው የዮዳሄ ልጅ በናያስ የሞዓባዊን የአሪኤልን ሁለቱን ልጆች ገደለ፤ በአመዳይም ወራት ወርዶ በጉድጓድ ውስጥ አንበሳ ገደለ።


ሁሉም ጽኑዓን ኃያላንና በሠራዊቱ ላይ አለቆች ነበሩና በአደጋ ጣዮቹ ጭፍሮች ላይ ዳዊትን አገዙት።


አንዳንዱም በመልካም መሬት ወደቀ፤ አንዱም መቶ፥ አንዱም ስድሳ፥ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ።


የፀሓይ ክብር አንድ ነው፤ የጨረቃ ክብር ሌላ ነው፤ የከዋክብት ደግሞ ሌላ ነው፤ የአንዱም ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ክብር ይለያል።