እርሱ ግን ተነስቶ እጁ እስኪዝልና ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን ወጋ፤ በዚያችም ዕለት ጌታ ታላቅ ድልን አደረገ። ሕዝቡም ከእርሱ በኋላ ምርኮ ለመግፈፍ ብቻ ተመለሰ።
1 ዜና መዋዕል 11:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱና ዳዊት በእርሻውም መካከል ጸንተው ቆሙ፤ ስፍራውንም አላስደፈሩም፥ ፍልስጥኤማውያንንም ገደሉ፤ ጌታም በታላቅ ድል አድራጊነት አዳናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ በዕርሻው መካከል ቦታ ይዘው ስለ ነበረ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤ እግዚአብሔርም ታላቅ ድል ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱና ተከታዮቹ በዚያው በማሳው ውስጥ ፍልስጥኤማውያንን ተቋቊመው ወጉአቸው፤ እግዚአብሔርም ታላቅ ድልን አጐናጸፋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሻውም መካከል ቆመው ጠበቁት፥ ያችንም ቦታ አዳናት፤ ፍልስጥኤማውያንንም ገደላቸው፤ እግዚአብሔርም በታላቅ ማዳን አዳናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሻውም መካከል ቆመው ጠበቁት፤ ፍልስጥኤማውያንንም ገደሉ፤ እግዚአብሔርም በታላቅ ማዳን አዳናቸው። |
እርሱ ግን ተነስቶ እጁ እስኪዝልና ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን ወጋ፤ በዚያችም ዕለት ጌታ ታላቅ ድልን አደረገ። ሕዝቡም ከእርሱ በኋላ ምርኮ ለመግፈፍ ብቻ ተመለሰ።
እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቆዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር።
እርሱ ከዳዊት ጋር በፈስደሚም ነበረ፥ በዚያም ገብስ በሞላበት እርሻ ውስጥ ፍልስጥኤማውያን ለውጊያ ተሰብስበው ነበር፤ ሕዝቡም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ።
ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው ዳዊት ወዳለበት ወደ ዓለቱ ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ፤ የፍልስጥኤማውያንም ሠራዊት በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።
ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን የገደለው በገዛ ሕይወቱ ቆርጦ ነው። ጌታ ለመላው እስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም አይተህ ደስ አለህ። ታዲያ እርሱን በከንቱ በመግደል ዳዊትን በመሰለ ንጹሕ ሰው ላይ ለምን በደል ትፈጽማለህ?”