1 ዜና መዋዕል 1:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ፥ ቲምናዕ፥ አማሌቅ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች፤ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም፣ ቄኔዝ፣ ቲምናዕ፣ አማሌቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤሊፋዝም ቴማን፥ ኦማር፥ ጸፊ፥ ጋዕታም፥ ቀናዝ፥ ቲምናዕና፥ ዐማሌቅ ተብለው የሚጠሩትን ልጆች ወለደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ሳፍር፥ ጎታም፥ ቄኔዝ፥ ቴምናስ፥ አማሌቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ፥ ቲምናዕ፥ አማሌቅ። |
ስለዚህ ጌታ በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፤ በእውነት የመንጋው ትንንሾች እንኳ ይጐትቷቸዋል፤ በእውነት የማደሪያቸውም በረት በእነርሱ ላይ ይሣቀቃል።