ኤርምያስ 49:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ስለዚህ ጌታ በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፤ በእውነት የመንጋው ትንንሾች እንኳ ይጐትቷቸዋል፤ በእውነት የማደሪያቸውም በረት በእነርሱ ላይ ይሣቀቃል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶም ላይ ያቀደውን፣ በቴማን በሚኖሩትም ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፤ ታናናሹ መንጋ ተጐትቶ ይወሰዳል፤ በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸውን ፈጽሞ ያጠፋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ስለዚህም በኤዶም ሕዝብ ላይ ያቀድኩትንና በቴማን ከተማ ሕዝብ ላይ ላደርግ የፈለግኹትን ስሙ፤ ልጆቻቸው እንኳ እንደ በግ ግልገሎች እየተጐተቱ ይወሰዳሉ፤ በእነርሱም ምክንያት የሚያያቸው ሁሉ ይደነግጣል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ስዎች ላይ ያሰባትን ዐሳብ ስሙ፤ ትንንሾች በጎችን ዘርፈው ይወስዷቸዋል፤ የሚኖሩባትንም ማደሪያቸውን ባድማ ያደርጉባቸዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፥ በእውነት የመንጋ ትንንሾች ይጐተታሉ፥ በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል። Ver Capítulo |