በሁለተኛውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም አፈሩ፤ ተቀደሱም፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።
ዘኍል 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህ ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊዜው አድርጉት፤ እንደ ሥርዓቱ ሁሉ እንደ ፍርዱም ሁሉ አድርጉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዓሉንም በዚህ ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ በተወሰነው ሕግና ሥርዐት መሠረት ሁሉ አክብሩ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ፥ በተወሰነለት ጊዜ ታደርጉታላችሁ፤ እንደ ሥርዓቱ ሁሉ እንደ ደንቡም ሁሉ ታደርጉታላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት በሕጉና በሥርዓቱ መሠረት ሥርዓቱን ይፈጽሙ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊዜው አድርጉት፤ እንደ ሥርዐቱ ሁሉ እንደ ፍርዱም ሁሉ አድርጉት።” |
በሁለተኛውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም አፈሩ፤ ተቀደሱም፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።
ካህናቱም በሚበቃ ቍጥር ስላልተቀደሱ፥ ሕዝቡም ገና በኢየሩሳሌም ስላልተሰባሰቡ፥ በጊዜው ያደርጉት ዘንድ አልቻሉምና ንጉሡና አለቆቹ የኢየሩሳሌምም ጉባኤ ሁሉ በሁለተኛው ወር ፋሲካውን ያደርጉ ዘንድ ተመካክረው ነበር።
እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።